ዕለቱ ማክሰኞ የካቲት 26 , 2011 ዓ/ም ምሽት ላይ ነበር
የዳጉ የሚድያ ፌስቲቫልና አዋርድ ፤ የዳጉ ጋዜጠኞች ወርሃዊ መድረክ ትኩረቱን “ሴትነት እና ሚድያ በኢትዮጵያ” ላይ አድርጎ ቦሌ በሚገኘው ሞዛይክ ሆቴል በድምቀት ሲካሄድ በክብር እንግድነት ከተገኙት ውድ ሴት ኢትዮጵያዊያን መካከል ፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ደርባባዋና ፍልቅልቋ ጋዜጠኛ እሌኒ መኩሪያ አንዷ ነበሩ።
መድረኩ ላይ እንዲገኙ በስንት ውትወታ አማላጅ የላኩት የእርሳቸውን ልጅ በሸገር ሬዲዮ የሚተላለፈው “አፍሪካዊያን” ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ Qetselawork Seifu ን ነበር ፤ እርሳቸውም አላሳፈሩንም መድረኩ ላይ ተገኝተው የጋዜጠኝነት ህይዎት ልምዳቸውን ሳይሰስቱ አካፈሉን። እኛም አመሰገንናቸው፤ አከበርናቸውም። ምናልባትም ይህ መድረክ የመጨረሻቸው መድረክ ሳይሆን አይቀርም።
እርሳቸው ያኔ መድረክ ላይ ሲፍለቀለቁ ባልደረባዬ Tekle Markon በካሜራው ምስላቸውን አስቀርቶ ነበር ፤ አጋረሁዋችሁ።
“ዞሮ ዞሮ ከቤት ፤ ኖሮ ኖሮ ከመሬት ነውና !” ጋዜጠኛ እሌኒ መኩሪያ ህልፈታቸውን ሰማን። ሀገራችንን በቅንነት ስላገለገሉ ከልብ እናመሰግንወታለን። ለወዳጅ ዘመድ ሁሉ መፅናናት ይሁን ። ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ !
1 Comment
Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.